08/10/2025
የድሮ ጴንጤዎች ትህትናቸው ማራኪ ነበረ። ሲሰድቧቸው ሲያንጓጥጧቸው አካላዊ ጥቃት ቢደርስባቸው እንኳ "እፀልይልሃለው" ይሉ ነበረ። በእርግጥ አሁን በስነምግባራቸው የሀይማኖታቸውን እሴት የሚሰብኩ እጅግ ብዙ ናቸው። ጥቂቶች ላይ የሚታየው የትንኮሳ ተግባር ብዙሃኑን አይወክልም። ነገር ግን እንዲህ አይነት የመንገድ ላይ ሰባኪ የሀይማኖቱ ተከታዮች እረፉ ሊላቸው ይገባል። መከባበር ያስፈልጋል። ስብከት ሞራል፣ ትህትና እና መተናነስ እንጂ ማንጓጠጥና መተንኮስ አይደለም።
ሙክታሮቪች