
11/03/2025
ማንም የማንንም ኃይማኖት የማንቋሸሽና የመዝለፍ መብት የለውም። ይሄ ሁሉንም ኃይማኖቶች የሚመለከት ነው። አንድ ተሳዳቢ የ'ርሱ ያልሆነን እምነት ሲያንቋሽሽ ስንሰማ መገሰጽ እና እንዲያርፍ ማሳሰብ እንጂ ማዳመቅ እና ማዳነቅ ከየትኛውም ኃይማኖት አስተምህሮ ያፈነገጠ ነው።
ከዚህ ቀደም የኦርቶዶክስ ኃይማኖትን እና ተከታዮችን ሲያንቋሽሹ የነበሩ 'ተራ' ግለሰቦች ገስጸናል፤ አልገራ ሲሉም ለሕግ እንዲቀርቡ ጮኸናል፤ ወደፊትም የምናደርገው ነው።
ይሄ ሰለሞን ሽፈራው የተባለ ግለሰብ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ.) በነው^ረኛ ቃላት ሲያንጓጥጥ ዝም መባሉ እንዳለ ሆኖ ጭራሽ ጥብቅና የሚቆሙለት መኖራቸውን ማየት ያማል። ይሄ ነው^ረኛ ግለሰብ ለሕግ እንዲቀርብ መተባበርና እንደ'ርሱ ያሉ ሥርዓት አልበኞች ጥፋት እንዳይደግሙ መማሪያ እንዲሆኑ ነበር መትጋት ያለብን። እንዴት ሆኖ ነው በጥቂት ጋጠ-ወጦች ምክንያት እንዲህ ለመባባል የደረስነው?
ይህ ግለሰብ በእስልምና ኃይማኖት ተከታዮች ዘንድ ሊታለፍ የማይገባ ድንበር አልፏል፤ አልፏል ብቻ ሳይሆን በአስጸያፊ ሁኔታ በነብያችን (ሰ.0.ወ.) ተሳልቋል። እናም ለፍርድ ቀርቦ ቅጣቱን ማግኘት አለበት። ለዚህም ጥረት እያደረጉ ካሉ ወንድም እህቶቼ ጎን መቆሜን እና የሚጠበቅብኝ ለማድረግ ዝግጁ መሆኔን ለማሳወቅ እወዳለሁ። ክርስትያን ወንድም እህቶችም ለተገቢ ፍትህ ከጎናችን እንደሚቆሙ በጽኑ አምናለሁ።