23/07/2025
ጀግናው አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴና ባለሀብቱ ኢ/ር ቢጃይ ናይከር ተገናኙ🤝
| ቆይታ ከጀግናው አትሌት በኢ/ር ቢጃይ እንዲህ ተፅፏል✍️
ጭዌ....
ሜላት ሃይሌ ገ/ሥላሤ (የሃይሌ ልጅ) እና Abayomi Rotimi Mighty (ናይጄሪያዊ ጸሐፊ) 'Dissecting Haile ' የሚል አሪፍ መጽሐፍ ጽፈዋል።
በሃይሌ ህይወት፣ሥራ፣ተሞክሮ ወዘተ ዙሪያ በደንብ ተከትቧል። በርግጥ ሃይሌ ተገልጦ የማያልቅ የህይወት ዘመን ተሞክሮዎች አሉት። ጥዋት ባለቤቱን ደርባባዋን ወ/ሮ አለም ተቻለንና ሁለቱን ሤቶች ልጆቹን በሚደንቅ ቅልጥፍናው ቤሮዬ ይዞ ከች አላለም ? አወጋን... ተጫወትን።ቴክኖሎጂ ይመሥጠዋል።አብሮ የመሥራት ኦፈሮችም አሉት።
"ሃይሌ እሥቲ የሥራ መርሆዎችህን ንገረኝ? ጀማው ይከየፍ፣ ይነሣሣ፣ጭማቂ ተሞክሮ ያግኝበት፣በት በት፣ተፍ ፣ተፍ ይቅዳበት" አልኩት።
"ዌል እንግዲህ"...አለ ከጭላሎ ተራራ ጀርባ እንደወጣች ጸሃይ በደመቀው ፍጹም ፈገግታ ታጅቦ።
"
1- በል...Discipline and Hard Work ያሥፈልጋል ግብረገብነት እና ትጋት ማለት ነው ።“Business is like running. You have to train every day.” ሁሌ ሠልጥን እራሥህን አብቃ።
2-በል ...Start Small, Grow Steadily ያሥፈልጋል በትንሹ ጀምር ቀሥ ብለህ እደግ “I started with one building, now I have many.”ይገርምሃል።
3-በል...Invest in Ethiopia ሃገሬን በሥራ ማሣደግ እፈልጋለሁ“I want to change Ethiopia through business, not just charity.”
4-በል...Respect for Workers and Community ያሥፈልጋል... ሠራተኞችህን እና የአካባቢህን ማህበረሠብ አክብር “My workers are part of my team, like in running.”
5-በል...Learn from Others ከሌሎች መማር ጥሩ ነው።
“I travel, I watch, I learn.”
6-በል...Staying Humble and Authentic ጨዋ እና ሃቀኛ ሁን።ሁሌም መርሆ ይሁኑህ።
7-በል...Diversification ያሥፈልጋል በተለያዩ ሃገርን በሚጠቅምና በሚያዋጣ ሥራዎች ውሥጥ ተሠማራ።ሆቴል፣ሪዞርት፣ቡና፣ት/ቤት፣ሥፖርት መዓከል፣ሪል እሥቴት፣ግብርና፣መአድን፣ ወዘተ ውሥጥ በመግባት ሪሥክንም መቀነሥ ይሆናል።
8-በል...Avoid Corruption and Stay Honest ሥርቆትን ተጸየፍ በአቋምህ ጽና ። በነጻ አእምሮ ተወዳደር።አቅምህ እሡ ነውና።
9.እንደአለም ጠንካራ ሚሥት ይኑርህ፣እንደነሜላት የተባረኩ የተመረቁ ልጆች ፈጣሪ ይህጥህ። "
ይህን ያለው ጀግናው ሃይሌ ገ/ሥላሤ ነው። መጽሃፉ በተለያዩ ቋንቋዎች እየተተረጎመ ነው። አንብቡት ብዙ አሪፍ አሪፍ ጉዳዮችን ይዟል።
እኔ ደግሞ እላችኋለሁ....
"you can't build a business ,until you've built your self" ...self discovery is important ።እራሥህን አግኝ።ራሥህን አብቃ።