AbichoEthio

AbichoEthio Ethiopian Brodcasting Media��

🥹🥹🥹ወንድሟ ሂጃብ ሳትለብሺ ቲክቶክ ላይ ለምን ቪዲዮ ትለቂያለሽ ብሎ የደበደባት ቲክቶክ ላይ queen of Djibouti በመባል የምትታወቀው የሱማሌ እህታችን ምን አስተያየት አላችሁ ? ሴት...
17/07/2023

🥹🥹🥹

ወንድሟ

ሂጃብ ሳትለብሺ ቲክቶክ ላይ ለምን ቪዲዮ ትለቂያለሽ ብሎ የደበደባት

ቲክቶክ ላይ queen of Djibouti በመባል የምትታወቀው የሱማሌ እህታችን

ምን አስተያየት አላችሁ ?

ሴት ልጅ እንደዚህ ማድረግ አግባብ ነውንስ ?

እንዴት ታዩታላችሁ ግን ኢትዮጵያውያን ? ? ?

😎😎😎

🌴🌴🌴

ልብ ሰባሪ መረጃ❗ በሀዋሳ ከተማ በታቦር ተራራ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዋን ዘርፈው፤ ወደ ገደል ወረወሯት።*****ወጣት ሄለን ታሊሞስ ሁሉም የሚያቃት የሚመሰክርላት የዋህ ቅን ለታናናሾቿ ሳይቀር የ...
10/07/2023

ልብ ሰባሪ መረጃ❗

በሀዋሳ ከተማ በታቦር ተራራ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዋን ዘርፈው፤ ወደ ገደል ወረወሯት።
*****

ወጣት ሄለን ታሊሞስ ሁሉም የሚያቃት የሚመሰክርላት የዋህ ቅን ለታናናሾቿ ሳይቀር የምትታዘዝ እግዚአብሔርን የምትፈራ በቤተሰቦቿም በጓደኞቿም የተወደደች የተመሠገነች ልጅ ናት።

ሄለን በ2013 ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በኤሌክትሪካል ምህንድስና እና በጤና መኮንንነት የመጀመሪያ ዲግሪዋን ጨርሳለች።

ሁለተኛ ዲግሪዋን በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ እየተማረች ሳለ፥ አንድ ቀን ለመዝናናት ከተማሪ ጓደኞቿ ጋር ሀዋሳ ታቦር ተራራ በሄደችበት የቀን ጎዶሎ፥ በዘራፊዎች እጅ ትወድቃለች።

ያላትን ሁሉ ወስደው፤ ከታቦር ተራራ ወደ ታች ገፍትረው ጣሏት። ከፍተኛ ጉዳት ደረሰባት፥ ሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ገባች። ሁለት ጊዜ ጭንቅላቷን ኦፒራሶን እንደተደረገች አባቷ ተናግሯል።

አሁን ሄለን ኮማ ውስጥ ናት።

ከሰኔ 4 ቀን 2015 ጀምሮ ለቤተሰቦቿ የህክምና ወጪ ከአቅማቸው በላይ ሆነ።

እናንት ደጋግ ኢትዮጵያዊያን
ይህችን ቅን ወጣት ለማዳን እንረባረብ።

Talimos Tadesse Gebeyo (አባት)
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
የሂሳብ ቁጥር
1000270955828

Kylian Mbappé አባቱ በተወለደበት ሀገር ካሜሩን ሲያርፍ በአድናቂዎች አቀባበል ተደርጎለታል 🇨🇲
07/07/2023

Kylian Mbappé አባቱ በተወለደበት ሀገር ካሜሩን ሲያርፍ በአድናቂዎች አቀባበል ተደርጎለታል 🇨🇲

አርባምንጭ ከተማ ወደ ከፍተኛ ሊግ ወርዷል!2014 ላይ ዳግም ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተመልሶ ሲሳተፍ የነበረው አርባምንጭ ከተማ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ለገጣፎ ለገዳዲን ተከትሎ ከሁለት ተ...
06/07/2023

አርባምንጭ ከተማ ወደ ከፍተኛ ሊግ ወርዷል!

2014 ላይ ዳግም ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተመልሶ ሲሳተፍ የነበረው አርባምንጭ ከተማ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ለገጣፎ ለገዳዲን ተከትሎ ከሁለት ተከታታይ የተሳትፎ ዓመታት በኋላ ወደ ከፍተኛ ሊግ መውረዱ ተረጋግጧል።

https://t.me/joinchat/QHDEnL36tPdttINg

👆👆 መረጃዎቻችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻነላችንን ይቀላቀሉ

እሱ እድሜው 87 ነውእሷ ደግሞ  85 አመቷከተማ ውስጥ በየመንገዱ ዳር የሚታዩት እጇን በእጁ ይዞ ሲሄዱ ነው"ለምንድነው ሁልጊዜ እጇን ይዘሃት የምትዞረው?" ሰዎች ይጠይቁታል"የመርሳት በሽታ ...
06/07/2023

እሱ እድሜው 87 ነው
እሷ ደግሞ 85 አመቷ

ከተማ ውስጥ በየመንገዱ ዳር የሚታዩት እጇን በእጁ ይዞ ሲሄዱ ነው

"ለምንድነው ሁልጊዜ እጇን ይዘሃት የምትዞረው?" ሰዎች ይጠይቁታል

"የመርሳት በሽታ አለባት" ይመልሳል

"ታዲያ እጇን ለቅቀሃት ትተሃት ብትሄድ ታውቃለች?"

"ኧረ በጭራሽ አታውቅም! እኔ እንኳ ምኗ እንደሆንኩኝ ረስታኛለች" ባል ይመልሳል

"ጭራሽ አንተንም አታስታውስህም?" መንገደኛ ይጠይቃል

"አዎን ለ53 አመታት አብረን ኖረናል! አሁን ግን አታውቀኝም"

"ታዲያ የማታውቅህ ከሆነ ለምን አትተዋትም? ለምን እጇን ይዘህ ትዞራለህ ታዲያ?"

"እሷ ላታውቀኝ ትችላለች🤷🏽‍♂️እኔ ግን አውቃታለሁ! እሷ ረስታኝ ሊሆን ይችላል እኔ ግን አልረሳኃትም!"

❤️🙌🏼

በዘመለአክ እንድሪያስ

ለክቡር አቶ ሽመልስ አብዲሳየኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት ፊንፊኔ---------በሸኖ ከተማ በዎላይታ ተወላጆች ላይ እየተፈጸመ የሚገኘዉን አፈሳና ማፈናቀል እንዲያስቆሙልን ስለመ...
06/07/2023

ለክቡር አቶ ሽመልስ አብዲሳ
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት
ፊንፊኔ
---------
በሸኖ ከተማ በዎላይታ ተወላጆች ላይ እየተፈጸመ የሚገኘዉን አፈሳና ማፈናቀል እንዲያስቆሙልን ስለመጠየቅ
----------
ክቡር ሆይ--በሸኖ ከተማ ዉስጥ በጉልበት ስራ ፣ በችርቻሮ እና ሌሎች underpaid businesses በመሰማራት ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ሕይወት የሚመሩ የዎላይታ ተወላጆችን በማንነታቸዉ መነሻ የከተማዉ ጸጥታ አካላት በሌሊት ከመኖሪያ ቤታቸዉ ቀን ከስራ ቦታቸዉ እያፈሰ በእስር ቤት አጉሯል ።
-------
በሌላ በኩል ትንንሽ ሕጻናትን(ለማሰር ዕድሜያቸዉ ያልደረሱትን) አፍሶ በመሰብሰብ በከተማዉ የትራፊክ ፖሊሶች አማካኝነት ወደ ፊንፊኔ የሚጓዙ ተሽከርካሪዎች ጭነዉ በመዉሰድ በፊንፊኔ -አዲስአበባ ከተማ ጎዳናዎች እንዲጥሏቸዉ ተደርገዋል።
----------
እስር ቤት ታጉረዉ ከቆዩት መካከል አብዛኛዎቹ ዛሬ ከሰዓት በፊት "ከተማዉን ከስምንት ሰዓት በፊት ለቀው ለመሄድ፣ ዳግም በከተማዉ ላለመገኘት እያንዳንዳቸዉ ፈርመዉ እንዲወጡ የተደረገ ሲሆን ምናልባት ዳግም በከተማዉ የሚገኝ ግለሰብ እስራት ሳይሆን እስከ መግደል ድረስ እርምጃ እንደሚወሰድበት በማስጠንቀቅ፣ ከእስር ቤት ከመለቀቃቸዉ በፊት እያንዳንዳቸዉ አስቸኳይ ፎቶግራፍ ተነስተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል።
--------
ክቡር ፕሬዚዳንት ሆይ;- ከእስር ቤት ፈርመዉ ከወጡት መካከል አንዳንዶች ለከተማዉ የብልጽግና ፓርቲ ሃላፊ አቤቱታ አሰምተዉ ነበር። ሃላፊዉም" ሰርታችሁና ለፍታችሁ መኖር የሚከለክላችሁ የለም። ለማንኛውም የከተማዉን ጸጥታ ሃላፊ አናግሩት።" ባለዉ መሠረት ለጸጥታ ሃላፊዉ ቢሮዉ ድረስ በመሄድ እሮሮአቸውን ነግረዉታል።
ይሁንና የጸጥታ ሃላፊዉ " ዛሬ ከእስር ቤት ፈርማችሁ የወጣችሁ የወላይታ ብሔር ተወላጆች ከከተማዉ ዛሬ እስከ ስምንት ሰዓት ድረስ መዉጣት አለባችሁ።

ከስምንት ሰዓት በኋላ በከተማዉ ከተገኛችሁ በራሳችሁ ላይ ፈርዳችኋል።" ቤተሰብ +ልጆች ያለን እና ቋሚ ንብረት ያፈራን ሰዎች አለን። ለእኛ ምን ይሻለናል ብለዉ ሲጠይቁት፦ ኃላፊዉ "አያገባንም። ከከተማዉ ለቃችሁ እንድትወጡ በከተማ አመራር ደረጃ ተወስኗል።ያልተያዙ የዎላይታ ተወላጆችን ዛሬና ነገ በተለይም ከገበያ ለቃቅመን በመያዝ አስረን ፈቃደኛ ከሆኑ ዳግም በከተማዉ ላለመታየት አስፈርመን እንለቃቸዋለን።" የሚል ኃላፊነት የጎደለዉን ምላሽ ሰጥቷል።
--------
በመሆኑም በዚች ከተማ በወላይታ ተወላጆች ላይ በማንነታቸዉ መነሻ እየተፈጸመ ያለዉን ሕገመንግስታዊና ሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዲቆምና አፋጣኝ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ በተለይም ከሸኖ ከተማ forcefully deport ተደርገዉ ፊንፊኔ-አዲስአበባ ከተማ ወርዉረዉ ለአደጋ ለተጋለጡት የዎላይታ ተወላጅ ሕጻናት ተገቢ የመፍትሔ እርምጃ ይፈለግላቸዉ ዘንድ ትዕዛዝዎ ለሚመለከታቸዉ አካላት ያስተላልፉ ዘንድ በአክብሮት አሳስባለሁ።

Justice to ethnic Wolaita migrants!
ከአክብሮት ሰላምታ ጋር
አሰፋ ወዳጆ ኦያቶ ነኝ።
share share to all concerned.

«በስልክ ደውሎ 200ሺ ብር አዘጋጅ ሲሉ ቀልድ ነበር የመሰለኝ» አንዱ በስልክ ደውሎ 200ሺ ብር አዘጋጅ አለኝ! ቀልድ ስለመሰለኝ "ብሩን እንዴት ላቀብላችሁ?" ብዬ መለስኩለት "አንተ ብቻ ...
05/07/2023

«በስልክ ደውሎ 200ሺ ብር አዘጋጅ ሲሉ ቀልድ ነበር የመሰለኝ»

አንዱ በስልክ ደውሎ 200ሺ ብር አዘጋጅ አለኝ! ቀልድ ስለመሰለኝ "ብሩን እንዴት ላቀብላችሁ?" ብዬ መለስኩለት "አንተ ብቻ ብሩን አዘጋጅ እኛ እንዴት እንደምንቀበል እናውቃለን፣ በአምስት ቀን ውስጥ አዘጋጅ" ብለው ስልኩ ተዘጋ።

እኔ ቀልድ ስለመሰለኝ ረስቼዋለሁ እነሱ የገቢ ምንጬን ሁሉንም ነገር አጥንተው ነበር እኔ ግን ስለ እነሱ ምንም አላውቅም። በስድስተኛው ቀን ጠዋት ከቤት እንደወጣው አምቡላንስ የሚመስል መኪና መጥቶ አጠገቤ ቆመ ከመኪናው ውስጥ ሰዎች ወረዱ "ይቅርታ፣ ይቅርታ" እያሉ የኋላ በር ከፍተው አሰገቡኝ ራሴን ለማዳን ብሞክርም አልቻልኩም ይላል።

ቀዝቃዛ ከነበረችው ከተማ ወስደው በጣም ሞቃማ ወደ ሆነ ስፍራ ወስደው በአንድ ቆርቆሮ ቤት አስገቡኝ ይላል ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ ባለታሪኩ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ሲናገር የባንክ ATM ተቀበሉኝ ፓስወርዱን ወሰዱ ከዛ የቤት እና የመኪና ቁልፌን ተቀበሉኝ ብሏል።

እዛ በቆየውበት ወቅት አፋኞቹ የፖለቲካም ይሁን የብሄር ነገር አልነበረም እነሱ ሲጠይቁኝ የነበረው 200ሺ ብሩን እንድሰጣቸው ነበር ብሏል።

በመጨረሻም ፊቴን እና አፌን አፍነው የከተማ መግቢያ ላይ ጥለውኝ ሄዱ በቆየውበት 10 ቀናት ዳቦ እና ሙዝ ነበር የሰጡኝ ውሃ ብዙ ስላላገኘው ደሜ ወርዶ ነበር።

ታፍኜ በተወሰድኩ ጊዜ ወንዝ ውስጥ ሲፈልጉኝ ነበር ሌላው ታፍኖ ነው ነው ተብሎ ከእኔ ጋር ግኑኝነት የነበራቸው ሰዎች ታስረው ነበር የጠበቁኝ ይላል። አፋኞቹ ምንም አይነት መረጃ እንዳልናገር ከተናገርኩ እንደሚገድሉኝ ነበር አስጠንቅቀው የለቀቁኝ በአሁኑ ጊዜ ከሚኖርበት ከተማ ለቆ በሌላ ከተማ እንደሚገኝ ነው የተናገረው።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት  "የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል" 12ኛው የኢትዮጵያ ክልል እንዲሆን ወሰነወላይታ ሶዶ፤ ሰኔ 28/ 2015  (ወቴቪ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት "የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች...
05/07/2023

የፌዴሬሽን ምክር ቤት "የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል" 12ኛው የኢትዮጵያ ክልል እንዲሆን ወሰነ

ወላይታ ሶዶ፤ ሰኔ 28/ 2015 (ወቴቪ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት "የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል" 12ኛው የኢትዮጵያ ክልል እንዲሆን ወሰነ።

ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ፤ “የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል” የሚል ስያሜ የተሰጠውን ክልል ለመመስረት የማንነት፣ የአስተዳደር ወሰንና የሰላም ግንባታ ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ በሙሉ ድምጽ አፅድቋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ውብሸት አየለ የሕዝበ ውሳኔውን አጠቃላይ ሂደት ሪፖርት ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።

በዚህም በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ሕዝቦች ክልል ስድስት ዞኖች (በጋሞ፣ በጎፋ፣ በወላይታ፣ በጌዴኦ፣ በኮንሶና በደቡብ ኦሞ) እንዲሁም አምስት ልዩ ወረዳዎች (በቡርጂ፣ በአማሮ፣ በደራሼ፣ በባስኬቶ እና በአሌ) በጋራ “የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል” የሚመሰርቱ ይሆናል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Address

Rustenburg

Website

https://youtube.com/@abichoethio5228

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when AbichoEthio posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share