08/07/2025
Happy Birthday!
መልካም ልደት!
እንኳንም ተወለድ
➙አትሌት አበበ ቢቂላ ይባላል!!
➙ ኦለፒያን ነው
➙ የኢትዮጵያ የማራቶን አባት!!!!
➙ ለእስካሁን ላሉ የዘመናችን አትሌቶች ፈር ቀዳጅ ከመሆን ያለፈ ታሪክ ያለው ፤ኢትዮጵያ የመሮጥ አቅም እንዳላት አይደለም ማሸፍ እንደምትችልም ለአለም ህዝብ በታላቁ ኦሊምፒክ የገለጠ የመጀመሪው የኢትዮጵያ ባለ ክብር አትሌት ነው።
➙ ማራቶንን በባዶ እግሩ መሮጡ ደግሞ ሌላ ግርምት የፈጠረ አትሌት ነው።
➙አትሌቱ በኢንተርናሽናል ደረጃ እ ኤ አ ከ1960 እስከ 1968 ለ8 አመት በሩጫ ላይ ቆይቶ 10 ውድድሮችን አድርጓል።
በተደጋጋሚ ብዙ የሮጠቻቸው ርቀት ማራቶን ነው 9 ጊዜ ሮጧል። 10ሺህ ሜትርን 1 ጊዜ በጀርመን በርሊን ISTAF, Berlin እ ኤ አ በ1962 ሮጦ 29:00. 8h PB በመሮጥ
2ኛ ደረጃን አግኝቶ ጨርሷል።
ዘጠኝ ማራቶን የሮጠባቸው ቦታዎችና የገባባቸው ሰዓቶች
➙ሮም ኦሊምፒክ OG, Roma እ ኤ አ 10 Sep 1960 የገባበት ሰዓት 2:15:16 PB ያገኘው ደረጃ 1ኛ
➙ግሪክ Athína እ ኤ አ 7 May 1961 የገባበት ሰዓት 2:23:44 ያገኘው ደረጃ 1ኛ
➙ ስሎቫኪያ Košice እ ኤ አ 8 Oct 1961 የገባበት ሰዓት 2:20:12 ያገኘው ደረጃ 1ኛ
➙አሜሪካ ቦስተን ማራቶን እ ኤ አ 1963 የገባበት ሰዓት 2:24:43 ያገኘው ደረጃ 5ኛ
➙ለቶኪዮ ኦሊምፒክ ማጣሪያ አዲስ አበባ ላይ ኦገስት 3/1964 የገባበት ሰዓት 2:16.18 ያገኘው ደረጃ 1ኛ
➙ ቶኪዮ ኦሊምፒክ OG, Tokyo እ ኤ አ 21 Oct 1964 የገባበት ሰዓት 2:12.11 PB ያገኘው ደረጃ 1ኛ
➙ ቶኪዮ ማራቶን እ ኤ አ 9 May 1965 የገባበት ሰዓት 2:22:55 ያገኘው ደረጃ 1ኛ
➙ ሴኡል ማራቶን እ ኤ አ 30 Oct 1966 የገባበት ሰዓት 2:17:04 ያገኘው ደረጃ 1ኛ
➙ሜክሲኮ ኦሊምፒክ OG, México
እ ኤ አ 20 Oct 1968 DNF (አቋረጠ)
➙ ሀገሩ ኢትዮጵያን 3 ጊዜ በኦሊምፒክ ወክሏል። በ3 ጊዜ ውክልናው 2 ወርቅ ወስዷል።
በኦሊምፒክ ታሪክ ማለትም እ ኤ አ ከ1956 እስከ 2024 በተካሄዱ ኦሊምፒኮች ከኢትዮጵያዊን አትሌቶች ውስጥ ለሀገሩ ብዙ ሜዳሊያዎችን በማግኘት በሁለት ወርቅ 6ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ኢትዮጵያ በኦሊምፒክ ታሪክ 39 ሜዳሊያዎችን አግኝታለች ለእኔ ሰለሳ ዘጠኙም ሜዳሊያ የአበበ ቢቂላ ነው ብዬ ነው የማምነው።
Photo
Abebe Bikila on the podium of the 1964 Tokyo Olympics, after winning gold in the marathon, and surrounded by Basil Heatley of Great Britain (Silver) and Kokichi Tsuburaya of Japan (Bronze
📌ኢትዮ ራነርስ ለኦሊምፒክ ጀግኖች ትልቅ ክብር አለው!!
🇪🇹1960 Gold Abebe Bikila Men's marathon
10 September 2:15:16.2 Rome
🇪🇹 Tokiyo Gold Abebe Bikila Men's marathon 21 October
ዛሬ የጀግናው የፈርቀዳጁ የማራቶን አባት አትሌት አበበ ቢቂላ ልደት ነው
አትሌቱ በዛሬዋ ቀን እ ኤ አ 7 August 1932 ተወለደ።
እ ኤ አ ✝ 25 October 1973 ከዚህ አለም ድካም አረፈ!!!
Happy Birthday!
መልካም ልደት!
እንኳንም ተወለድክ!!
የአበበ ቢቂላ አድናቂ የሆነችሁ በሙሉ እስኪ እንኳንም ተወለድክ በሉት!!
መልካም ልደት!!
💣🥳💖
💣🥳💖
Happy Birthday!
መልካም ልደት!
እንኳንም ተወለድክ!!
መረጃዎች የተጠናከሩበት ገፆች
wikipedia and world athletics pages
Photo Via Getty Images
Wondmagegn Getachew Yigezu