Prosperity For All

Prosperity For All News

Gore-Mattu Airport 🎈🎈
08/08/2026

Gore-Mattu Airport 🎈🎈

የአለም ሚዲያዎች ስለኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ እየተነጋገሩ ነውበአንድ ጀምበር 805 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል የተመዘገበው ታሪካዊ ስኬት የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃንን ቀልብ በመሳብ ኢትዮጵ...
04/08/2026

የአለም ሚዲያዎች ስለኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ እየተነጋገሩ ነው

በአንድ ጀምበር 805 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል የተመዘገበው ታሪካዊ ስኬት የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃንን ቀልብ በመሳብ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረክ የአየር ንብረት ለውጥ ተሟጋች አድርጓታል። ወደ 26 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች በነቂስ በመውጣት ያሳዩት የማይበገር የአንድነትና የባለቤትነት ስሜት፣ ሀገራችን በራሷ አቅም የተፈጥሮ ሀብቷን የመንከባከብና የደን ሽፋኗን የማሳደግ ጽኑ አቋም እንዳላት ለዓለም ያስመሰከረ አበይት ኩራት ነው።

ዓለም በከባድ የበረሃማነትና የአየር ንብረት መዛባት ስጋት ውስጥ በምትገኝበት በዚህ ወሳኝ ወቅት፣ ይህ የኢትዮጵያ ግዙፍ የችግኝ ተከላ ንቅናቄ ለአፍሪካም ሆነ ለተቀረው ዓለም አርአያ የሚሆን ተግባራዊ መፍትሔ አሳይቷል። በሀገር ውስጥ ከተከናወነው በተጨማሪም የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር በመተባበር መርሃ ግብሩን በዓለም አቀፍ ደረጃ ማካሄዳቸው፣ ሀገራችን ለምድር ጤናማነትና ለዘላቂ ልማት ያላትን መሪነትና ቁርጠኝነት በግልጽ የሚያረጋግጥ ነው።






01/08/2026
01/08/2026
🚨 የጥፋት ጥምረትና የግብዝነት ፖለቲካ፡ የኢህአፓ እና የህወሓት አደገኛ ሸፍጥ! 🚨በታሪክ አጋጣሚ ሀገርንና ትውልድን የፈጁ ኃይሎች ዛሬም እንደገና የሰላም ተቆርቋሪ መስለው ብቅ ብለዋል!ኢህአ...
23/07/2026

🚨 የጥፋት ጥምረትና የግብዝነት ፖለቲካ፡ የኢህአፓ እና የህወሓት አደገኛ ሸፍጥ! 🚨

በታሪክ አጋጣሚ ሀገርንና ትውልድን የፈጁ ኃይሎች ዛሬም እንደገና የሰላም ተቆርቋሪ መስለው ብቅ ብለዋል!

ኢህአፓ «መንግሥት በትግራይ ጦርነት ሊቀሰቅስ ነው» በማለት የሚያሰማው የሐሰት ጩኸት፣ ከህወሓት ጋር ያለውን አጥፊና የሴራ ፖለቲካ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ግልጽ ማስረጃ ነው። ሁለቱም ቡድኖች በታሪካቸው በጽንፈኝነት፣ በዜሮ ድምር እሳቤ እና የጥፋት መንገድ የተከተሉ የትርምስና የውድመት ምንጮች ናቸው።

ትናንት ትውልድ ያስፈጀው ኢህአፓ፣ ዛሬ ሀገር ካደማው ህወሓት ጋር ተሻርኮ የሚያሰማው የግብዝነት አቋም የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ሽፋን በማድረግ ሀገርን ዳግም ወደ ጦርነት እና ግጭት ለመክተት የተሸረበ ትልቅ የፖለቲካ ሸፍጥ ነው!

⚠️ ከታሪክ ያልተማረ የጥፋት አካሄድ፦ የኢህአፓ ታሪካዊ ስህተት

ኢህአፓ በ1960ዎቹ በደርግ መንግሥት ላይ የ«ነጭ ሽብር» አዋጅ በመክፈት ሀገሪቱን የማያባራ ሰቆቃና ሽብር ውስጥ እንድትገባ አድርጓል። ድርጊቱ ለሀገራችን ያተረፈው ጥፋት በጥቂቱ፦
የምሁራንና የወጣቶች እልቂት፣ የማይሽር የታሪክ ቁስል፣የመከራ ጥሪ አስከትላል።

📢 የዛሬው ስጋትና ጥሪያችን!
አሁንም ባለው የፖለቲካ ሁኔታ፣ ከትላንቱ የጥፋት ታሪካቸው ያልተማሩና በህዝብ ሰላምና ደህንነት ላይ አዲስ ችግር ለመፍጠርና ሁከት ለማስነሳት የተሰለፉ አካላት አሉ!

❌ ከታሪክ መማር ያቃተው፣ ሀገርንና ህዝብን ለአደጋ የሚያጋልጥ ይህ ኋላቀር አስተሳሰብ ዳግም በሀገራችን ቦታ ሊኖረው አይገባም!

👉 የሀገራችንን ሰላም የሚረብሹና የሴራ ፖለቲካቸውን የሚያስፋፉ ማናቸውንም ሕገ-ወጥ እንቅስቃሴዎች ነቅተን ልንታገላቸውና በጋራ ልንቆምባቸው ይገባል!

Address

Adwa
Metu

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Prosperity For All posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Prosperity For All:

Shortcuts

Share