29/07/2026
ከመቐለ 👏
የሙያ ክብር እና የሰብአዊነት ጥግ!
ሕግን በጀግንነት እያስከበረች፣ ሰብአዊነትንና የልብ ርህራሄን በተግባር ያረጋገጠችው ድንቅ የሕዝብ አለኝታ — ምክትል ሳጅን ቅጣቱ በኛ!
በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በሚሰጥበት ወቅት የተመደበችበትን የፀጥታ ማስከበር ተልዕኮ በብቃትና በጀግንነት እየተወጣች ነበር። ነገር ግን አገልጋይነቷ በፖሊስ የደንብ ልብሷ ላይ ብቻ አልተወሰነም።
ልጇን የሚይዝላት አጥታ የተጨነቀችውን ተፈታኝ እናት ችግር በቅንነት ከተረዳች በኋላ፣ ከተሰጣት የስራ ኃላፊነት ጎን ለጎን ህፃኑን በእቅፏ አቅፋ በመያዝ የእናትነትና የሰብአዊነት እውነተኛ ትርጉምን አሳይታለች።
በዚህም ደግነቷ እናቲቱ ፈተናዋን በተረጋጋ መንፈስና ሙሉ በሙሉ በትኩረት እንድትፈተን ምክንያት ሆናለች።
ይህ ተግባር ከዩኒፎርም በላይ ትልቅ የርህራሄና የደግነት ልብ እንዳላት ማረጋገጫ ነው!
በጀግንነት መጠበቅ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!
ለዚህች ውድና ኩሩ የፖሊስ አባላችን የከበረ ምስጋናችንና አክብሮታችን ይድረሳት!
Via Ethiopia Federal Police
👏👏👏
ጉርሻ page
🌴🌴🌴