Habesha Prime

Habesha Prime ከተበደሉት ጎን ነን

"ለወጣቶች መልፈስፈስን አላስተምርም!" — ጋዜጠኛና የታሪክ ምሁር ታዲዮስ ታንቱ""እኔ ተፈጥሮ በሰጠችኝ የማመዛዘን ሕሊና መሠረት ለተበደሉ ወገኖች ሚዛናዊ ሀሳብ በመስጠቴ ምንም ዓይነት የጥፋ...
11/09/2026

"ለወጣቶች መልፈስፈስን አላስተምርም!" — ጋዜጠኛና የታሪክ ምሁር ታዲዮስ ታንቱ"

"እኔ ተፈጥሮ በሰጠችኝ የማመዛዘን ሕሊና መሠረት ለተበደሉ ወገኖች ሚዛናዊ ሀሳብ በመስጠቴ ምንም ዓይነት የጥፋተኝነት ስሜት አይሰማኝም። በጠበቆቼ በኩል ማቅለያ ለፍርድ ቤቱ እንዳቀርብ የቀረበልኝን ጥያቄ አልተቀበልኩትም።

ምክንያቱም የቅጣት ማቅለያ ማዘጋጀት ማለት 'አጥፍቻለሁ' የሚል የጥፋተኝነት አቋምን የሚያሳይ በመሆኑ፣ ተፈጥሮ የፈቀደችልኝን መብት በሕግ አልቀይረውም!

የሰናፍጭ ቅንጣት የምታክል ወንጀል ስለሌለብኝ ውሳኔውን አልቀበለውም! ፍርድ ቤቱ የፈለገውን ይወሰን፤ እኔ በዚህ ዕድሜዬ (በ74 ዓመቴ) ለወጣቶች መልፈስፈስንና አንገት መድፋትን አላስተምርም!"

(ይህ ኃይለኛና ወጥ አቋም የገለጡበት ንግግር ታዲዮስ ታንቱ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀርበው የፍርድ ማቅለያ እንዲያቀርቡ በተጠየቁበት ወቅት የተናገሩት ነው፦ ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም) ፅናት፣ እውነት እና ዋጋ መክፈል!

እውነትን በመናገራቸው፣ ግፈኞችን በመቃወማቸው እና ለተበደሉ ወገኖች ድምፅ በመሆናቸው ብቻ ለዓመታት የወህኒ ቤት መሪር እንግልት ያስተናገዱት የእውነት አባት ጋሽ ታዲዮስ ታንቱ የታሰሩበትን የግፍ ጊዜ ጨርሰው በቅርቡ ይፈታሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ስለ እውነት በመቆማቸው "አሸባሪ" የሚል ታርጋ ቢለጠፍባቸውም፣ ለአቋማቸውና ለሕሊናቸው ያልተንበረከኩ የዘመናችን የፅናት ምልክት ናቸው!

ጋሽ ታዲዮስ ታንቱ — ባሉበት መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልዎ!
ፅናትዎ ለአዲሱ ትውልድ ትልቅ ትምህርት ነው!

ሰላም ለኢትዮጵያ
ሰላም ለህዝባችን
ወሎ አዲስ የህዝብ አድማስ

"ቀን ጣለው ብሎ ወንድሙን ያልካደው ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ" ያስተላለፉት የደስታ መልዕክት"ለክርስቲያን ታደለ እና ለተፈቱት ወንድምና እህቶቻችን የቀረበ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት እንኳን ...
11/09/2026

"ቀን ጣለው ብሎ ወንድሙን ያልካደው ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ" ያስተላለፉት የደስታ መልዕክት"

ለክርስቲያን ታደለ እና ለተፈቱት ወንድምና እህቶቻችን የቀረበ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት

እንኳን እግዚአብሔር አስፈታህ ክሪስ ወንድሜ! ሌሎችም አብረዋችሁ የተፈታችሁ ወንድሞችና እህቶቻችን፣ ለቤታችሁና ለወዳጅ ዘመዶቻችሁ እግዚአብሔር በሰላም አበቃችሁ።

እስካሁንም በእስር ላይ የሚገኙት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የነፃነት አየር ተንፍሰው፣ በቅርቡ ከሚወዷቸው ቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲቀላቀሉ አሁንም ጸሎታችንና ምኞታችን ነው ሲል ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ መልዕክቱን በሶሻል ሚድያ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል።

"ቀን ጣለህ ብሎ ወንድሙን ያልካደ፣ በእያንዳንዱ የፓርላማ መድረክ ድምፅ ሆኖ 'ፍቱት!' እያለ ስለ ፍትህ የተከራከረለት የቁርጥ ቀን ወንድሙ ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ፤ ለተከበረው ወንድሙ ክርስቲያን ታደለ የነፃነት አየር በመተንፈሱ የተሰማውን ጥልቅ ደስታና የእንኳን አደረሰህ መልዕክት በታላቅ ፍቅርና አክብሮት አስተላልፏል።"

:
:
ሰላም ለኢትዮጵያ
ሰላም ለህዝባችን
ወሎ አዲስ የህዝብ አድማስ

  Ethiopia is celebrating New Year’s Day as the country officially enters 2019 under the Ethiopian calendar. The calenda...
11/09/2026

Ethiopia is celebrating New Year’s Day as the country officially enters 2019 under the Ethiopian calendar. The calendar is about seven to eight years behind the Gregorian calendar and has 13 months.

  ኢትዮጲያ እየመጣች ነው  🔥🔥🔥
11/09/2026

ኢትዮጲያ እየመጣች ነው 🔥🔥🔥

  በዚህ ሰአት በመላው ኢትዮጲያ ተጠባቂው የነጎድጎዱ ዳኘ ዋለ ሙዚቃ በጉጉት እየተጠበቀ ነው
11/09/2026

በዚህ ሰአት በመላው ኢትዮጲያ ተጠባቂው የነጎድጎዱ ዳኘ ዋለ ሙዚቃ በጉጉት እየተጠበቀ ነው

11/09/2026

ደብረማርቆስ | አማራ | ኢትዮጲያ
የበዐል ገበያ 💚💛❤

የሙዚቃው ንጉስ
10/09/2026

የሙዚቃው ንጉስ

  ጀግናው የአማራ የፓለቲካ ቁንጮ ክቡር አቶ ክርስትያን ታደለ  መፈታቱ ተሰማ አቶ ክርስትያን ሌሎች የቀድሞ የፓርቲ ጎዶቹ ለመንግስት በመገበር ሲኖሩ እሱ ግን በህዝብ ተመርጦ በፓርላማ አማራ...
10/09/2026

ጀግናው የአማራ የፓለቲካ ቁንጮ ክቡር አቶ ክርስትያን ታደለ መፈታቱ ተሰማ አቶ ክርስትያን ሌሎች የቀድሞ የፓርቲ ጎዶቹ ለመንግስት በመገበር ሲኖሩ እሱ ግን በህዝብ ተመርጦ በፓርላማ አማራን ያስከበረ ጀግና መሆኑን ማሳየቱ ይታወሳል።

የኢትዮጲያ የፓለቲካ ድምቀቱ እንኳን ወደ ሰፊው አስር ቤት መጣህ።

መሪ አልባዋ ከተማ።
10/09/2026

መሪ አልባዋ ከተማ።

ደብረ ማርቆስ አውሮፕላን ማረፊያ የምንሰራ መኪኖች ላይ ከተማ አስተዳደሩ ሆን ብሎ ባቆማቸው ሰወች እየተዘረፍን ነው።

#ፍኖተሰላም |ኤርፖርት ሄደን ሰው ለማድረስ ሆነ ለመጫን ሰንትራ ብሎ ራሱን የሰየመ ማህበር ነኝ የሚል 300 ብር በቢያጆ(በአንድ ዙር) እየተቀበለን ይገኛል ለደላላ በሚል 200 በድምሩ 500 ብር በቢያጆ ይወስዱብናል እኛ ይህንን ለማካካስ ስንል ህዝቡ ላይ የትራንስፖርት ዋጋን እየጨመርን እንገኛለን።

ህዝባችን ኖሮት ሳይሆን በፀጥታ ስጋት ምክንያት ከፍተኛ ወጭ በማውጣት በአውሮፕላን ሲሄድ እኛ ከከተማ አውሮፕላን ማረፊያ እየጠየቅነው ያለ ብር ከፍተኛ ነው ይህ የሆነው እነዚህ ስብስቦች በቢያጆ 500 ብር ስለሚቀበሉን ነው።

በየትኛው የሀገሪቱ አውሮፕላን ማረፊያ ነው ግለሰብ ማህበር ነኝ በማለት ያለምንም ፈቃድ በቢያጆ 500 ብር የሚቀበል ???

ባህር ዳርን ብትወስድ አውሮፕላን ማረፊያ ለመግባት 10 ብር ነው የሚከፈል አዲስ አበባም በቆየህበት ሰአት ተሰልቶ ከ20 ብር ጀምሮ ነው ክፍያ የደብረ ማርቆሱ ሰንትራ ማኅበር ይህንን ያህል ብር ክፈሉ የሚል ኤርፖርቱን የገነባው እርሱ ነው ????

ደብረ ማርቆስ ከተማ ትራንስፖርት ሎጅስቲክ ፅ/ቤት ከዚህ ስብስብ ጋር የጥቅም ትስስር ሳይኖራቸው አይቀርም ህጉ በማይፈቅድበት ህዝብን ቆሞ ሲዘረፍ ማየት ተባባሪነት ወይንም የጥቅም ተጋሪነት ከመባል የዘለለ ነገር አይኖረውም።

የአማራ ክልል ትራንስፖርት ሎጅስቲክ ቢሮ ይህንን ልክ ያልሆነ ድርጊት ሊመረምር ሊያረም ሊያስቆም ይገባል ሲሉ መልዕክት አድርሰውናል።
ምንጭ》የሹፌሮች አንደበት

ፍኖተሰላም

Address

Addis Abeba
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Habesha Prime posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share