Shagiz computer

  • Home
  • Shagiz computer

Shagiz computer Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Shagiz computer, .

እስልካችንን በዝግታ የሚገድሉ እና እድሜውን የሚያሳጥሩ  ዋና ዋና ምክንያቶች እነሆ ፦📌 1) ኦሪጅናል ያልሆኑ (Cracked/Mod) አፖችን መጫን ፦ ብዙ ጊዜ የሚከፈልባቸውን አፖች ወይም ጌ...
18/02/2026

እስልካችንን በዝግታ የሚገድሉ እና እድሜውን የሚያሳጥሩ ዋና ዋና ምክንያቶች እነሆ ፦

📌 1) ኦሪጅናል ያልሆኑ (Cracked/Mod) አፖችን መጫን ፦ ብዙ ጊዜ የሚከፈልባቸውን አፖች ወይም ጌሞች በነፃ ለማግኘት ስንል ከማይታወቁ ድህረ-ገጾች ላይ የምናወርዳቸው አፖች (APK) ዋናው የስልካችን ጠላቶች ናቸው ። [ ጉዳት የለላቸው ጠቃሚ mod app ቢኖሩም ]

🎯 ጎጂው App ግን ስልኩን ያለምንም ምክንያት ያሞቀዋል ፣ ባትሪው በሰከንድ ውስጥ ያልቃል፣ እንዲሁም የእርስዎ የግል መረጃ (ፎቶ፣ የባንክ መረጃ) ለሌላ ሰው ተላልፎ ይሰጣል ።

📌 2) ስቶሬጅን (Storage) እስከ ጫፍ መሙላት 🙄፦ ስልኩ ላይ ነፃ ቦታ ሲጠፋ ሲስተሙ ለመንቀሳቀስ ይቸገራል፤ ይህም ፕሮሰሰሩ እንዲሞቅና ስልኩ እድሜው እንዲያጥር ያደርገዋል ።

[ ስልኩን የሚገልና ቀርፋፋ የሚያደርግ አንዱ ምክንያት ቢያንስ ከስልኩ space 10% ክፍት አድርጉ ስልኩ በደንብ እንዲሰራ ]

📌 3) ስልክን "Restart" አለማድረግ ፦ ስልክን ለረጅም ጊዜ አጥፍቶ አለመክፈት በውስጡ ትናንሽ የሶፍትዌር ስህተቶች (በ ቴክኖሎጂ ቋንቋው Bugs ) እንዲከማቹ ያደርጋል፤ ይህም ስልኩን ያደክመዋል ።

[ ቢያንስ በሳምንት ስልካችሁን restart አድርጉ ...]

📌 4) ከባድ ጌሞችን በተለይ ስልኩ በሙቀት እየጋለ መጫወት ፦ ከፍተኛ ሙቀት የባትሪ እና የውስጣዊ ክፍሎች (Motherboard) አንደኛ ጠላት ነው ። ሙቀት የስልኩን ዕድሜ በግማሽ ይቀንሳል።

📌 5) ርካሽና ኦሪጅናል ያልሆኑ ቻርጀሮች ፦ ወጥ የሆነ የኤሌክትሪክ ፍሰት ስለማይሰጡ የስልኩን የኃይል መቆጣጠሪያ ክፍሎች ቀስ በቀስ ያቃጥላሉ ።

📌 6) . የዩኤስቢ (USB) ኬብሉ ጥራት ፦ ጥሩ ቻርጀር ቢኖራችሁ እንኳ ኬብሉ ደካማ ከሆነ ኤሌክትሪኩን በትክክል አያስተላልፍም። ስልክዎ ቻርጅ ለማድረግ ከ 3 ሰዓት በላይ የሚፈጅ ከሆነ፣ ኬብሉን መቀየር ነው ።

በታዋቂ የፓስወርድ ማስተዳደሪያ መተግበሪያዎች ላይ ከፍተኛ የደህንነት ስጋት መገኘቱ ተገለጸበሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የዲጂታል መረጃዎቻቸውን ሚስጢር ለመጠበቅ የሚጠቀሙባቸው ታዋቂ የፓስወርድ ማ...
17/02/2026

በታዋቂ የፓስወርድ ማስተዳደሪያ መተግበሪያዎች ላይ ከፍተኛ የደህንነት ስጋት መገኘቱ ተገለጸ

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የዲጂታል መረጃዎቻቸውን ሚስጢር ለመጠበቅ የሚጠቀሙባቸው ታዋቂ የፓስወርድ ማስተዳደሪያ (Password Managers) መተግበሪያዎች ለከፍተኛ አደጋ መጋለጣቸዉን አንድ አዲስ ጥናት አመለከተ።

በስዊዘርላንድ የሚገኙ የኢቲኤች ዙሪክ (ETH Zurich) እና የዩኤስአይ (USI) ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ይፋ ባደረጉት የጥናት ውጤት መሰረት፤ በቢትዋርደን (Bitwarden)፣ ላስትፓስ (LastPass)፣ ዳሽሌን (Dashlane) እና ዋን ፓስወርድ (1Password) መተግበሪያዎች ላይ 27 የሚሆኑ ጥቃት ማድረሻ ክፍተቶች መገኘታቸዉን ገልጿል።

ተመራማሪዎቹ እንዳስታወቁት፣ እነዚህ ክፍተቶች የአገልግሎት ሰጪ ተቋማቱ ሰርቨሮች በመረጃ መንታፊዎች (Hackers) እጅ ቢወድቁ፣ ተጠቃሚው ሳይያውቅና ሳይጠረጥር የተቀመጡ ፓስወርዶችን ለማየትና ለመቀየር ዕድል የሚሰጡ ናቸው።

በጥናቱ ከተካተቱት መተግበሪያዎች መካከል ከፍተኛው ስጋት የተመዘገበው በቢትዋርደን (Bitwarden) ላይ ሲሆን፣ ድርጅቱ 12 የደህንነት ክፍተቶች ተገኝተውበታል።

በመቀጠልም ላስትፓስ 7፣ ዳሽሌን 6 እንዲሁም ዋን ፓስወርድ 2 የጥቃት ክፍተቶች እንደተገኙባቸው ተገልጿል።

በተለይም በቢትዋርደን ላይ የተገኘውና "ማሊሸስ ኦቶ-ኤንሮልመንት" የተባለው የጥቃት ዘዴ፣ አንድ ተጠቃሚ ወደ ድርጅት አካውንት እንዲቀላቀል ግብዣ በሚላክለት ወቅት ጠላፊዎች መሃል በመግባት የተጠቃሚውን ዋና ቁልፍ (Master Key) ሰርቆ መውሰድ የሚያስችል መሆኑ በምሳሌነት ቀርቧል።

ይህም ጠላፊዎች የግለሰቡን ሙሉ መረጃ ያለምንም እንቅፋት እንዲቆጣጠሩ ያደርጋቸዋል።

ምንም እንኳ የሳይበር ደህንነት ተመራማሪዎቹ ተጠቃሚዎች በአሁኑ ወቅት ከመጠን በላይ ሊሰጉ እንደማይገባ ቢገልጹም፣ አገልግሎት ሰጪ ተቋማቱ ግን የተገኙትን ክፍተቶች ለመድፈን አስቸኳይ የጥገና ስራና የማሻሻያ (Updates) እርምጃዎችን መጀመራቸውን አስታውቀዋል።

ማንኛውም የእነዚህ መተግበሪያዎች ተጠቃሚ መረጃውን ከጥቃት ለመከላከል መተግበሪያዎቹን በየጊዜው ማዘመን (Update ማድረግ) እና ባለ ሁለት ደረጃ ማረጋገጫ (2FA) መጠቀም ወሳኝ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች አሳስበዋል።

አዲስ ስልክ ለመግዛት ሲያስቡ እነዚህን ነጥቦች የግድ ይፈትሹ!ስልክ መግዛት ዝም ብሎ ፎቶ ማየት ወይም ብራንድ መምረጥ አይደለም። የገንዘብዎ ዋጋ እንዲመለስልዎትና ለረጅም ጊዜ እንዲያገለግልዎ...
17/02/2026

አዲስ ስልክ ለመግዛት ሲያስቡ እነዚህን ነጥቦች የግድ ይፈትሹ!

ስልክ መግዛት ዝም ብሎ ፎቶ ማየት ወይም ብራንድ መምረጥ አይደለም። የገንዘብዎ ዋጋ እንዲመለስልዎትና ለረጅም ጊዜ እንዲያገለግልዎት የሚከተሉትን 7 ወሳኝ ነጥቦች ልብ ይበሉ፦

1) ፕሮሰሰር (Processor)፦ የስልኩ "አንጎል" ነው። ስልኩ እንዳይቆራረጥ (Lag እንዳያደርግ) ጠንካራ ፕሮሰሰር ያለው መሆኑን ያረጋግጡ። ለምሳሌ ለጌም ወይም ለከባድ ስራ Snapdragon ወይም Apple Bionic የተሻሉ ናቸው።

2) ራም (RAM)፦ ስልኩ በአንድ ጊዜ ብዙ አፖችን የመክፈት አቅሙን ይወስናል። ዛሬ ላይ ቢያንስ 6GB ወይም 8GB RAM ያለው ስልክ መግዛት ለፍጥነትዎ አስተማማኝ ነው።

3) ስክሪን (Display Quality) ፦ ቀኑን ሙሉ የምናየው ስክሪኑን ስለሆነ AMOLED ወይም OLED ስክሪን ያላቸውን ይምረጡ። ቀለማቸው ጥራት ያለውና ለዓይን የማይደክሙ ናቸው።

4) ባትሪ (Battery Life) ፦ ከቻርጅ ጋር ተጣብቀው መኖር ካልፈለጉ ቢያንስ 5000mAh ባትሪ ያለውና Fast Charging (በፍጥነት ቻርጅ የሚያደርግ) መሆኑን ያረጋግጡ ።

5) ካሜራ (Camera Quality) ፦ የሜጋፒክሰል (MP) ብዛት ብቻውን ጥራት አይሰጥም ። በዩቲዩብ ላይ የስልኩን የካሜራ "Sample" ቪዲዮዎች በማየት ትክክለኛ ጥራቱን ያረጋግጡ ።

6) ስቶሬጅ (Internal Storage) ፦ ዛሬ ላይ አፖችና ፎቶዎች ትልቅ ቦታ ስለሚይዙ ቢያንስ 128GB ያለው ስልክ ይመረጣል ። "Memory Full" ከሚል ጭንቀት ያርፉበታል ።

7) የገበያ ዋጋ ፦ ሁሌም ዋጋውን ካሰቡት በጀት ጋር አገናዝቡ። አንዳንድ ጊዜ በስሙ ብቻ ... ውድ ከሆነ ስልክ ይልቅ፣ በተመሳሳይ ዋጋ የተሻለ አቅም (Specs) ያላቸው ሌሎች ብራንዶችን ማግኘት እንደሚቻል ታሳቢ አድርጉ።

🎯 አንድ ሚስጥር ፦

ስልክ ከመግዛታችሁ በፊት 'Google' ላይ በመግባት የስልኩን ስም ጽፋችሁ መጨረሻ ላይ 'GSMarena' ብላችሁ ፈልጉ። ስለ ስልኩ እያንዳንዱን ዝርዝር መረጃ (Specs) እዚያ ላይ በግልጽ ታገኛላችሁ!

Hp Core i7 1TB storage Hp G3Core i.78GB Ram1TB storageBattry life 3:00 hrsprice inboxhttps://t.me/getushagiz96
17/02/2026

Hp Core i7 1TB storage
Hp G3
Core i.7
8GB Ram
1TB storage
Battry life 3:00 hrs

price inbox
https://t.me/getushagiz96

አጭር የኢትዮ ቴሌኮም ኮዶች
16/02/2026

አጭር የኢትዮ ቴሌኮም ኮዶች

16/02/2026

ጋር Mohammed Seid – ከእነሱ ዋና አድናቂዎች እንደ አንዱ ሆኜ አሁን እውቅና አግኝቻለሁ!

የተኛውን ተጠቀማችሁት ታውቃላችሁ?
14/02/2026

የተኛውን ተጠቀማችሁት ታውቃላችሁ?

📶 Wireless LAN (WLAN)A Wireless LAN (WLAN) is a Local Area Network where devices communicate without cables, using wirel...
14/02/2026

📶 Wireless LAN (WLAN)

A Wireless LAN (WLAN) is a Local Area Network where devices communicate without cables, using wireless signals (Wi-Fi) instead of Ethernet cables.

It’s commonly used in homes, schools, offices, and campuses to allow multiple devices to connect to the network and internet.

🔹 Key Features

Uses Wi-Fi signals to connect devices.

Covers a small area (like a building or campus).

Provides mobility for devices within range.

Easy installation compared to wired LANs.

🔹 Components of a Wireless LAN

Wireless Router / Access Point (AP) – Sends and receives Wi-Fi signals.

Wireless Devices – Laptops, smartphones, tablets, desktops.

Modem – Connects WLAN to the ISP for internet access.

ISP (Internet Service Provider) – Provides internet service.

🔹 WLAN Diagram

Explanation:

Devices like laptops, smartphones, and desktops connect to the wireless router via Wi-Fi.

The router connects to the internet for external access.

እነዚህን አጫጭር ነስልክ ኮዶች እና ዌብሳይቶች በመጠቀም ብዙ መረጃወችን ታገኛላችሁ።
12/02/2026

እነዚህን አጫጭር ነስልክ ኮዶች እና ዌብሳይቶች በመጠቀም ብዙ መረጃወችን ታገኛላችሁ።

አማዞን ስቱዲዮ የቴሌቪዥን እና የፊልም ፕሮዳክሽኑን ውጤታማነት ለማሳደግ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለመጠቀም አቅዷል፡፡ እንደ ሮይተርስ ዘገባ አማዞን የሰውሰራሽ አስተውሎትን ቴክኖሎጂን በፊልም ...
11/02/2026

አማዞን ስቱዲዮ የቴሌቪዥን እና የፊልም ፕሮዳክሽኑን ውጤታማነት ለማሳደግ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለመጠቀም አቅዷል፡፡

እንደ ሮይተርስ ዘገባ አማዞን የሰውሰራሽ አስተውሎትን ቴክኖሎጂን በፊልም እና በቴሌቪዥን ዝግጅቶቹ በመጠቀም የፕሮግራሞቹን ጥራት ለማሳደግ እና ወጪን ለመቀነስ አቅዶ እየሰራ ነው።

ይህ የአማዞን ስቱዲዮ ዕቅድ የይዘት ፈጠራን በማፋጠን በስርጭት ፉክክር ውስጥ የላቀ የተወዳዳሪነት ጥቅምን ያስገኛል።

በሂደቱም በቅድመ ፕሮዳክሽን በኤ.አይ የታገዘ የስክሪፕት ትንተና እና የታሪክ ቅደም ተከተል ሰሌዳ ማመንጨት ያስችላል። በቀረጻ ወቅት ደግሞ ምናባዊ ስፍራዎችን በመፍጠር ረገድ ለቀረጻ የሚውሉ የቦታ ወጪዎችን ይቀንሳል። በድህረ-ፕሮዳክሽን ኤ.አይ የድምጽ እና የምስል አርትዖትን ያፋጥናል።

ሂደቱ እየናረ ያለውን የይዘቶች በጀት በመቆጣጠር ወጪ ቆጣቢ አማራጭ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ጉግል የአፍሪካ ቋንቋዎችን በሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ለማሳደግ ያለመ አዲስ የድምፅ መረጃ ስብስብ ይፋ አደረገ፡፡ጉግል ከአፍሪካ የምርምር ተቋማት ጋር በመተባበር “WAXAL” የተሰኘ የ...
11/02/2026

ጉግል የአፍሪካ ቋንቋዎችን በሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ለማሳደግ ያለመ አዲስ የድምፅ መረጃ ስብስብ ይፋ አደረገ፡፡

ጉግል ከአፍሪካ የምርምር ተቋማት ጋር በመተባበር “WAXAL” የተሰኘ የንግግር ዳታሴት ይፋ ማድረጉን አስታወቀ። ይህ ዳታሴት እንደ ስዋሂሊ፣ ሃውሳ፣ ዮሩባ እና ሉጋንዳን የመሳሰሉ ከሰሃራ በታች የሚነገሩ 21 የአፍሪካ ቋንቋዎችን ያካተተ ነው።

የመረጃ ስብስቡ ዋነኛ ዓላማም ከዚህ ቀደም ጥራት ያለው የተጠናቀረ የድምጽ የቋንቋ ግብዓት ባለመኖሩ ምክንያት በስልኮች ላይ የሚገኙ ምናባዊ ረዳቶችን ከመሰሉ የድምፅ ቴክኖሎጂዎች ተጠቃሚ መሆን ያልቻሉ ከ100 ሚሊዮን በላይ ተናጋሪዎችን ተጠቃሚ ማድረግና የዲጂታል ክፍተቱን መሙላት ነው።

ይህ በጉግል የገንዘብ ድጋፍ ለሦስት ዓመታት የተከናወነ ፕሮጀክት 1,250 ሰዓታት የሚፈጅ የተፈጥሮ ንግግር እና የስቱዲዮ ቀረጻዎችን ይዟል።

መረጃ የማሰባሰቡን ስራ በግንባር ቀደምትነት የመሩት የተለያዩ የአፍሪካ የምርምር ተቋማት በመሆናቸው የመረጃው ባለቤትነትም በእነዚህ ተቋማት እጅ እንዲቆይ ተደርጓል። ይህም አፍሪካውያን ተመራማሪዎችና ተማሪዎች በውጭ ኩባንያዎች ላይ ጥገኛ ሳይሆኑ በራሳቸው ቋንቋ እንዲሁም አካባቢያዊ ዐውድ የራሳቸውን የቴክኖሎጂ መፍትሄዎች እንዲያበለጽጉ ያስችላቸዋል።

@ኤ.አይ

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Shagiz computer posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Shagiz computer:

  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share

0904475596

let us contact