Teenya Olluma

Teenya Olluma Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Teenya Olluma, Digital creator, 16, Harar.

14/09/2026

ሜሪቶክራሲ አዲስ መጽሐፍ መስከረም 7 በባሕር ዳር ይመረቃል።

14/09/2026
14/09/2026

በክልሉ የህዝቦችን አብሮነት በማሳደግ ሰላምን የማጽናት ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል - አቶ ቶፊቅ መሀመድ

በሀረሪ ክልል የሕዝቦችን የአብሮነት እሴትን በማጎልበት ሰላምን የማጽናት ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ቶፊቅ መሀመድ ገለጹ።

የቢሮ ኃላፊው በሰጡት መግለጫ እንዳሉት በክልሉ የህዝቦችን አብሮነት በማጠናከር የሰላም እሴት ግንባታን ለማጎልበት የተጀመረው ቅንጅታዊ ሥራ ይጠናከራል፡፡

የነዋሪዎችን የሰላም ባለቤትነትና የጸጥታ ኃይሎችን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ስራን በማጠናከር የክልሉን ሰላምና ደኅንነት ይበልጥ ማጠናከር ተችሏል።

ሕዝቡን ያሳተፈ የጸጥታ ሥራ በማከናወን ክልሉ የሰላም ደሴት እንዲሆን ተደርጓል ብለዋል።

በክልሉ ዘላቂና አስተማማኝ ሰላም እንዲኖር ለማስቻል የሰላም ሠራዊት አደረጃጀት ገንቢ ሚና እየተወጣ መሆኑንም አንስተዋል።

ሕዝቡን በንቃት በማሳተፍ ለእያንዳንዱ ጸረ ሰላም እንቅስቃሴ ከጸጥታ ኃይሎች ጋር በቅንጅት የሚሰራበት አውድ ተፈጥሯል ነው ያሉት።

ወንጀል ፈጽመው ለማምለጥ የሚሞክሩ ኃይሎችን በቀላሉ በመቆጣጠር በቅንጅት በመሥራት ውጤት መገኘቱን ገልጸዋል።

በቀጣይም የክልሉን የሰላም፣ የጸጥታና ደህንነት ሥራ በላቀ ደረጃ ለመፈጸም በቁርጠኝነት እየተሰራ ነው ብለዋል።

በዚህም የወንጀል ምጣኔን መቀነስ፣ የዜጎችን የሰላም ባለቤትነት ሚና ማላቅ፣ ልዩነቶችን በንግግር የሚፈታ ማኅበረሰብ በመፍጠር በሰላም እሴት ግንባታ ላይ በትኩረት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

ሕገ ወጥ ንግድና ኮንትሮባንድ፣ የመሬት ወረራና ሕገ ወጥ ግንባታ እንዲሁም ሌሎች ወንጀሎችን በመቆጣጠር የሕግ የበላይነት በዘላቂነት የሰፈነባት ክልል የማድረግ ራዕይ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

14/09/2026
14/09/2026
14/09/2026

Address

16
Harar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Teenya Olluma posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share