TkusNeger

TkusNeger TkusNeger is your one stop destination for all trending news and entertainment.
(2)

This is official page of TkusNeger.com, an Ethiopian based Medai/News website providing you latest Ethiopian News, Movies and Music Videos.
ትኩስ መረጃዎች፣ ኣዳዲስ ፊልሞችና የሙዚቃ ክሊፖች አንዲደርስዎት ፔጁን ላይክ ያድርጉት።

ማራማዊታ 300 ሺህ ብሩን ለአርቲስት ቤዛነሽ ትስጣት!!💔🙏ተወዳጇ አርቲስት ማራማዊት አባተ በፒኤስጂ እና አርሰናል ጨዋታ ፒኤስጂ ያሸንፋል ብላ 300ሺ ብር ቁማር መብላቷን ይፋ ማድረጓ ይታወ...
06/02/2026

ማራማዊታ 300 ሺህ ብሩን ለአርቲስት ቤዛነሽ ትስጣት!!💔🙏
ተወዳጇ አርቲስት ማራማዊት አባተ በፒኤስጂ እና አርሰናል ጨዋታ ፒኤስጂ ያሸንፋል ብላ 300ሺ ብር ቁማር መብላቷን ይፋ ማድረጓ ይታወቃል ። አርቲስቷ የቁማር ገንዘብ አካውንቴ ውስጥ እንዲገባ አልፈልግም፣ ቤተክርስቲያንም አይቀበለውም ምን ላድርገው?" ስትል ጠይቃለች ።

ይሄንኑ ተከትሎ ማራማዊት አሁን በችግር ላይ ለምትገኘው አንጋፋዋ አርቲስት ቤዛነሽ አያሌው ገንዘቡን እንድትሰጥ በርካቶች እየጠየቁ ይገኛል ። አጋጣሚ ዝም ብሎ የመጣ አለመሆኑን በመጥቀስ ፤ አንቺ ገንዘቡ "እጄን አይንካው" ብለሻል፤ እግዚአብሔር ደግሞ በኪነጥበብ ውስጥ የብዙዎቻችን እናት የሆነችውን የቤዛነሽን በር እንድታንኳኪ መንገድ እየመራሽ ነው ሲሉ ማራማዊት ለተቸገረችው ቤዛነሽ ብሩን ድጋፍ እንድታደርግ ሃሳብ አቅርበዋል ።

ይህንን 300 ሺህ ብር ለእናታችን ለቤዛነሽ አያሌው ብታበረክቺላት ፣ ለኪነጥበቡ ቤተሰብ ትልቅ ክብርና ኩራት ትሆኛለሽ። ለራስሽ ህሊና ማንም ሊሰጥሽ የማይችለውን ታላቅ ሰላምና በረከት ታገኚበታለሽ። ለእናታችን ቤዛነሽ በጭንቋ ቀን የደረስሽላት ውድ ልጅዋ ትሆኛለሽ።

አንጋፋዋ አርቲስት ቤዛነሽ ፤ በኢትዮጵያ ኪነጥበብ በተለይም በእናትነት ትወናዋና በድንቅ ብቃቷ ትታወቃለች ። ለብዙ ዓመታት ለህዝብ ሻማ የሆነችው አርቲስት ቤዛነሽ አያሌው መጠለያ አጥታ መቸገሯን ተናግራለች ። አሁን ያለሁበትን ችግር ከንቲባ አዳነች አበቤ ይወቁልኝ ፤ መልዕክቴን አድርሱልኝ ስትል ሀዘን በተቀላቀለ ስሜት በቲክቶክ ገጿ ሀሳቧን ማጋራቷ ይታወቃል ።

ለዚህም ይመስላል ማራማዊት በቁማር የበላችውን ገንዘብ በችግር ላይ ለምትገኘው አርቲስት ብትሰጥ ለኪነጥበቡም ሆነ ለህሊናዋ ትልቅ ትርጉም ይኖረዋል ። ከዚህ አንፃር በርካቶችም ገንዘቡን ለዚህች እናታችን እንዲሰጥልን ድምጻቸውን እያሰሙ ነው። ማርያማዊት ይህንን የወገን ጥሪ ሰምታ የሁላችንንም ልብ እንደምታስደስት እናምናለን!

05/31/2026

የንጉስ ሚስት ትጨፍረው የለ እንዴ

"ግሉኮስ እየተነቀለልኝ ካሜራ ፊት እቆም ነበር... አደራ የተሰጠኝ ፊልም ነው::"ተዋናይት ፅናት ተረፈ (ህዶቴ)ተዋናይት ፅናት በቅርቡ ተመርቆ ለእይታ በበቃው "ህዶቴ" በተሰኘው አዲስ ፊልም...
05/31/2026

"ግሉኮስ እየተነቀለልኝ ካሜራ ፊት እቆም ነበር... አደራ የተሰጠኝ ፊልም ነው::"

ተዋናይት ፅናት ተረፈ (ህዶቴ)

ተዋናይት ፅናት በቅርቡ ተመርቆ ለእይታ በበቃው "ህዶቴ" በተሰኘው አዲስ ፊልም ላይ ባሳየችው አስደናቂ ብቃት የብዙዎችን ቀልብመግዛት ችላለች።

የሴት ልጅ ግርዛትን ማጠንጠኛ ባደረገው በዚህ ፊልም ላይ ስላጋጠማት ፈተና፣ ስለከፈለችው የጤና መስዋዕትነትእና ስለ ገፀ-ባህሪዋ ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 'መሰንበቻ' ፕሮግራም አግኝቶ አነጋግሯታል።

✍️ ያልጠበቀችው እውነት እና አደራው፦

"ዳይሬክተር ሳሚ ስክሪፕቱን ሲሰጠኝ በማንበቤ በጣም ደስ ብሎኝ ነበር። ሆኖም የሴት ልጅግርዛት አሁን ላይ የቆመ ይመስለኝ ስለነበር መጀመሪያ ላይ አላመንኩም ነበር። ዳይሬክተሩ ግን "አደራሽን፣ ጥሩ አድርገሽ
እንድትወጪው እፈልጋለሁ" ብሎ ትልቅ ሀላፊነት እና አደራ ነው የሰጠኝ።"

✍️ በግሉኮስ የታጀበው ከባዱ ቀረፃ፦

"ስራው እጅግ ከባድ ነበር። መሀል አካባቢ ላይ በጣም ታምሜ አልጋ ይዤ ነበር። ግሉኮስ እየተሰጠኝ ነበር ቀረፃውንያካሄድነው።

✍️ ስሜትን የሚፈትነው ትዕይንት፦

"የፊልሙ ስራ ከባድ የስሜት መለዋወጦችን የሚጠይቅ ነበር። በተለይ ደግሞ የግርዛቱ ሲን ላይ
ስሰራ ሙሉ ጉልበቴን እና ኢነርጂዬን አሟጦ ነበር የጨረሰው።"

✍️ የአንድ ወር ጥብቅ ልምምድ ፦

"ማንኛውንም ስክሪፕት ስቀበል የወረቀት ላይ ስራን በጥንቃቄ መስራትእወዳለሁ። ለዚህ ፊልምም ለአንድ ወር ያህል ከዳይሬክተሩ ጋር ጥብቅ ልምምድ አድርገናል። አለባበሷን፣አረማመዷን፣ ምን ትወዳለች፣ ምን ትጠላለች የሚለውን በጥልቀት አጥንተን ነው ወደ ቀረፃ የገባነው።"

✍️ የነገው የ"ህዶቴ" ጉዞ፦

"ፊልሙ አለም አቀፍ ደረጃን ጠብቆ የተሰራ በመሆኑ የተነሳየተለያዩ አለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫሎች ላይ ይሳተፋል ብዬ ትልቅ ተስፋ አደርጋለሁ።

05/30/2026

ጋዜጠኛ ሶፎንያስ ዋሲሁንን በፀሎታችሁ አስቡት!!😭😳😭

ሮሚዮ እና ጁሌት ተጣሉብን እኮ 🙈
05/28/2026

ሮሚዮ እና ጁሌት ተጣሉብን እኮ 🙈

ተመስገን ለቤቴ በቅቻለሁ! መድኃኔዓለም ስለማረኝ፣ ለታላቁ ክብር ስላበቃኝ ደስስስስ ብሎኛል"🚨 "በቅርቡ በሰፊው መድረክ ኑዛዜዬን ትሰማላችሁ" — ጋዜጠኛ ሶፎኒያስ በይፋ ይቅርታ ጠየቀ!ለረጅም...
05/26/2026

ተመስገን ለቤቴ በቅቻለሁ! መድኃኔዓለም ስለማረኝ፣ ለታላቁ ክብር ስላበቃኝ ደስስስስ ብሎኛል"

🚨 "በቅርቡ በሰፊው መድረክ ኑዛዜዬን ትሰማላችሁ" — ጋዜጠኛ ሶፎኒያስ በይፋ ይቅርታ ጠየቀ!

ለረጅም ጊዜ ከሚዲያ ዓለም ርቆ የቆየው ጋዜጠኛ ሶፎኒያስ፣ ወደ ቤቱ መመለሱን አስመልክቶ ባስተላለፈው ልብ የሚነካ መልዕክት መላው የኢትዮጵያን ህዝብና አድናቂዎቹን ይቅርታ ጠይቋል።

📌 ከጋዜጠኛው መልዕክት የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች፦

"ተመስገን ለቤቴ በቅቻለሁ! መድኃኔዓለም ስለማረኝ፣ ለታላቁ ክብር ስላበቃኝ ደስ ብሎኛል" ብሏል።

"ወዳጆቼ፣ አድናቂዎቼና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ አንገታችሁን አስደፍቻችኋለሁና ከልባችሁ ይቅር በሉኝ" ሲል ጥሪ አቅርቧል።

እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በቅርቡ በሰፊው መድረክ ላይ ቀርቦ ኑዛዜውን እንደሚያሰማ እና ብዙ የሚናገረው ነገር እንዳለ ገልጿል።

ጋዜጠኛ ሶፎኒያስ መልዕክቱን የደመደመው "አትፍረድ ይፈረድብሃል" በሚል ከባድ ማሳሰቢያና ህዝቡ በጸሎት እንዲያስበው በመጠየቅ ነው።

💬 እናንተስ ምን ትላላችሁ? አስተያየታችሁን ኮሜንት ላይ አስቀምጡ!


ጋዜጠኛ ሶፎኒያስ

ጆን ዳንኤል (John Daniel) እና ዲላን ፔጅ (Dylan Page) ለምን እስካሁን አልተገናኙም? 🤔
05/23/2026

ጆን ዳንኤል (John Daniel) እና ዲላን ፔጅ (Dylan Page) ለምን እስካሁን አልተገናኙም? 🤔

ቆንጆ ሙሽራ ደሞ ልጇ ስታምር🥰
05/22/2026

ቆንጆ ሙሽራ ደሞ ልጇ ስታምር🥰

በአሁኑ ሰዓት ከየትኛውም የቱሪዝም ሚኒስቴር ይፋዊ በጀትና ዘመቻ በላይ፣ በራሱ የግል ጥረትና ተነሳሽነት ሀገሩን ለዓለም እያስተዋወቀ የሚገኘው ወጣቱ ቲክቶከር አዶናይ አስደናቂና ታላቅ ስራ እ...
05/21/2026

በአሁኑ ሰዓት ከየትኛውም የቱሪዝም ሚኒስቴር ይፋዊ በጀትና ዘመቻ በላይ፣ በራሱ የግል ጥረትና ተነሳሽነት ሀገሩን ለዓለም እያስተዋወቀ የሚገኘው ወጣቱ ቲክቶከር አዶናይ አስደናቂና ታላቅ ስራ እየሰራ ይገኛል። በቲክቶክ ብቻ ከ5.9ሚሊዮን በላይ ተከታዮችን ማፍራት የቻለው አዶናይ፣ እስካሁን ሀገራዊ ገጽታን ለመገንባትና የሀገር ውስጥ እምቅ የቱሪስት መስህቦችን ለማስተዋወቅ ሲያደርጋቸው የነበሩት ተከታታይ ጥረቶች ከፍተኛ ተፅዕኖ የፈጠሩ ነበሩ። ዛሬ ደግሞ ስራውን ይበልጥ ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገረበትን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ አስመዝግቧል፤ ይህም በአለም አቀፍ ደረጃ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተመልካቾች ያሉት ታዋቂውን የዜና እና የቲክቶክ ኮከብ ዲላን ፔጅን (Dylan Page) በራሱ ጥረትና ግብዣ ወደ ኢትዮጵያ ማምጣት መቻሉ ነው።
መንግስታዊ ተቋማት በሚሊዮን የሚቆጠር ከፍተኛ በጀት መድበውና ሰፊ መዋቅር ዘርግተው ሊያመጡት የሚችሉትን ትልቅ ዓለም አቀፍ ትኩረት፣ ይህ ወጣት ያለምንም የገንዘብ ድጋፍ ብቻውን ተንቀሳቅሶ ትልቅ ተፅዕኖ በመፍጠር እውን አድርጎታል። ይህ የአዶናይ አስደናቂ ስኬት በአሁኑ ዘመን የማህበራዊ ሚዲያ ዲጂታል ጉልበት ምን ያህል ማደጉን የሚያሳይ ከመሆኑም በላይ፣ ለአንዲት ሀገር በጎ ገጽታ ግንባታ የአንድ ወጣት ፅናት፣ ህልምና ቁርጠኝነት ተቋማት ካላቸው አቅም በላይ ትልቅና ፈጣን ለውጥ ማምጣት እንደሚችል በተግባር ያስመሰከረበት ታላቅ ክስተት ሆኗል።

በመጨረሻም አገባሽ😍
05/20/2026

በመጨረሻም አገባሽ😍

Address

San Jose, CA

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when TkusNeger posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to TkusNeger:

Share