02/10/2026
አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ "መጽሐፍ ቅዱስ ራሳችንን ይቅር ማለት እንዳለብን ያስተምራል።"
መጽሐፍ ቅዱስ ፦ 👇
"ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ኃጢአት ሊያስተሰርይ ማን ይችላል?" (ማር 2፥7)
"መተላለፉ ይቅር የተባለችለት ኃጢአቱም የተከደነችለት ምስጉን ነው።" (መዝ 32፥1)
"ምሥራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ ፥ ያን ያህል መተላለፋችንን ከእኛ አራቀ።" (መዝ 103፥12)
"ኃጢአቴንም ሁሉ ወደ ኋላህ ጥለሃል።" (ኢሳ 38፥17)
"ኃጢአታችንንም በባሕሩ ጥልቅ ትጥለዋለህ።" (ሚክ 7፥19)
"የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።" (1ኛ ዮሐ 1፥7)
"በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።" (1ኛ ዮሐ 1፥9)
መጽሐፍ ቅዱስ ራስህን ይቅር እንድትል ፈጽሞ አይነግርህም ፤ ይህን ስላላደረገም እግዚአብሔር ይመስገን።
ይቅርታ የሚመጣው ከአንተ ውጭ ነው ይኸውም ኃጢአት ከሠራህበት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።
ችግሩ እግዚአብሔር ይቅር ብሎህ አንተ ግን አሁንም ራስህን ይቅር ማለትህ አለመቻልህ አይደለም።
ችግሩ የእግዚአብሔር ይቅርታ በቂ እንዳልሆነ አድርጎ ማሰብ ነው። ኢየሱስ 80 በመቶውን ይቅርታ ሰጥቶህ ፣ የቀረውን 20 በመቶ አንተ እንድትጨርሰው አልተወልህም።
እግዚአብሔር ይቅር ሲል ፣ ሙሉ በሙሉ ነው ይቅር የሚለው። የራስህ ይቅርታ አያስፈልግህም ፤ የሚያስፈልግህ የእሱ ይቅርታ ነው።
በክርስቶስ ደግሞ ያንን 100% አግኝተሃል።