13/04/2024
መካሪዬ ውዱ ወንድሜ፣ኢንጂነር አብዱልቃድር በረመዳን ፆም ላይ ሆኖ ለገጠሯ እናቴና አባቴ የመንገድ ችግርን በመፍታት ስራ ላይ ውሎ ወደ ሰፈር እየተመለሰ እያለ በመኪና አደጋ ህይወቱ ካለፈና ፆም ይዞ አላህን ከተገናኘ ዛሬ 2 አመት ሞላ!!😭
እሱ ከሞተ በኋላ ተደጋጋሚ ወደገጠር ቀበሌያ በገባውባቸው አጋጣሚዎች ሁሉ በፊት በመንገድ ችግር ስሰቃይ የነበረው ህዝብ ሁሌም ስለሱ ያወራል…እሱ መንገድ ከፈተልን አላህ የጀነቱን መንገድ ይክፈትለት የሚሉት እናትና አባቶች ቁጥር ብዙ ነው…አሚንን ያ አላህ!!!
ያ ኢላህ🙏🙏🙏
ያረቢ አላህ አብዱ በኛ ዘንድ የተወደደ ነው ውደደው…ያረቢ ለሰዎች አዛኝና ቅን ሰው ነው እዘንለት…እኛ መስክረናል ጌታዬ ከጥላህ አድርገው ወንድማችንን!!
አላህ ሆይ! ከቀብር ቅጣት ጠብቀው፣ አላህ ሆይ ጀነትን ቀዳሚ ሽልማትህ አድርገው፣ ከደጋግ ሙእሚኖች ፈርጀውም፣በእዝነትህ ከጀሀነም ቅጣት ጠብቀው፣ ከለቀቀው የተሻለ መኖርን ለግሰው፣ትቷቸው ከሄደው ቤተሰቦቹ የተሻሉ ቤተሰቦችን ስጠው፡፡
አሚንን🤲🤲🤲