04/07/2026
ይህ ጉድ ሰምታችኋል
ሰሞኑን እግር ኳስ ተጨዋቹ እስማኤል ሳይባሪ ወደ ባየር ሙኒክ ያደረገውን የ55 ሚሊዮን ዶላር ዝውውር ከመፈጸሙ በፊት... 👀
በፒኤስቪ (PSV) እያለ በሳምንት 19,200 ዩሮ ብቻ ያገኝ ነበር። የዚህን ጊዜ ፍቅረኛው እሷ የምትፈልገውን የቅንጦት አኗኗር ሊያኖራት እንደማይችል ስለተሰማት አፍንጫህን ላስ ብላው ትሄዳለች።
ነገር ግን የባየር ሙኒክ ዝውውሩ ይፋ እንደተደረገ ሁሉም ነገር ተቀየረ! ወደ ባየር ሙኒክ ሲፈርም ሳምንታዊ ደሞዙ ይፋ ባይደረግም በትንሹ ከ100-150 ሺህ ዩሮ በሳምንት ይገመታል። ይሄ ደሞ በፊት ከሚያገኘው በፍጹም አይገናኝም።
የዚህን ጊዜ ነው የቀደመው ፍቅረኛው ስልኳን በረጅሙ የይቅርታ መልዕክቶች አጨናነቀችው፤ በቃ ሰይጣን አሳስቶኝ ነው። አጥፍቻለው ማረኝ ጂኒ ጃንካ አላት። የዚህን ጊዜ ሳይባሪ ግን ለአንዱም መልዕክት ምላሽ አልሰጠም።
እና
በምትኩ፥ ያኔ የላከችበትን የድሮውን አልመጥንህም "You don't afford me" ብላ የላከችለትን መልዕክቶቿን አሁን ከላከችው አዲሱ የይቅርታ ደብዳቤ ጋር በማያያዝ (Screenshot አድርጎ) ኢንተርኔት ላይ ለህዝብ ይፋ አደረገው ይባላል። 😆
ብቻ ስናጠቃልለው
የተሻለ ኑሮ ይገባኛል በሚል ሰበብ ራሳቸው ለገበያ አቅርበው የተሻለ አቅም ያለው ይውሰደኝ የሚሉ ሴቶች በዝተዋል። ሲጠየቁ የተሻለ ይገባኛል ይሉሀል። የተሻለማ ካሰብሽ ወጥረሽ ሰርተሽ ለራስሽ የተሻለ አድርጊ እንጂ የተሻለ ገንዘብ ያመጣ ይውሰደኝ አይነት ጨረታ እንደ እቃ ራስሽ ላይ አታውጪ።